የ ግል የሆነ

የ ግል የሆነ

ይህ ድህረ ገጽ ሼድሊይ ሀ/የተወ/የግ/ማ በኩል አገልግሎት ላይ የዋለ ሲሆን የተመዘገበ አድራሻው Addis Ababa, Bole sub city Woreda 3,H.No new kadister block 03, Street number 646 Adica Bulilding 5 flour (“እኛ”) ደንበኞቻችን ወይም የድህረ ገጻችን ጎብኚዎች ገጻችንን ሲጠቀሙ ወይም በበይነ መረብ አማካኝነት ከኛ ጋር ግኑኝነት ሲፈጥሩ ግላዊነታቸውን እንዲሁም የበይነ መረብ ደህንነታቸውን ለመጠበቅ ቁርጠኛ አቋም አለን፡፡

ይህ መመሪያ ከእርስዎ በኩል የሚደርሱንን ወይም በድረ-ገፃችን በኩል የሚሞሉትን ማንኛውንም የግል መረጃዎን ደህንነቱ እንደተጠበቀ እንደምናቆይ እና ይህን በሚመለከት የዩናይትድ ኪንግደም የበይነ መረብ ደህንነት ጥበቃ ህጎችን እና ደንቦችን ሙሉ በሙሉ እንደምናከብር እናረጋግጣለን። ድህረ ገጻችንን ሲጠቀሙ የሚሞሉት ወይም ለመላክ የመረጡት የግል መረጃ አያያዝን በሚመለከት ያለንን አሰራር ለመረዳት እባክዎ የሚከተለውን በጥንቃቄ ያንብቡ። የ SHEDELI ጨዋታዎች ድህረ ገጽን በwww.addisgames.com (የእኛ ድረ-ገጽ) በመጎብኘትዎ በዚህ ፖሊሲ ማእቀፍ ውስጥ የተገለጹትን ተግባራት ተቀብለው እንደተስማሙ ይታመናል፡፡

ከእርስዎ የምንሰበስበው የመረጃ አይነቶች

ድህረ ገፃችንን ከሚጎበኙ እና ከሚጠቀሙ ግለሰቦች የሚከተሉትን አይነት የግል መረጃዎችን ልንሰበስብ፣ ልናከማች እና ልንጠቀም እንችላለን፡፡

ድረ-ገጻችን ከእርሶ የሚሰበስበው መረጃዎች፡ በድረ-ገጻችን አማካይነት ወደ አገልግሎታችን ሲመዘገቡ፣ ሲገቡ ወይም የእውቂያ መጠይቅ ቅጽ ሲያስገቡ ፎርም መሙላት የሚጠይቅ ቢሆን የሚያካትታቸው መረጃዎች የርስዎን ስም፣ የመኖርያ አድራሻ፣ የኢሜይል አድራሻ እና ስልክ ቁጥር ሊያካትት ይችላል።

ድረ ገጻችን ሲጎበኙ ወይም ሲጠቀሙ ስለእርስዎ የሚሰበስበው የድርጊት መራጃን የሚጨምር ሲሆን በእያንዳንዱ ድረ-ገጻችን ላይ ያደረጉትን ጉብኝት በተመለከተ የሚከተሉትን መረጃዎች በቀጥታ እንሰበስባለን፡፡

  • የኢንተርኔት ፕሮቶኮል አድራሻዎ (IP address) ፣ የአሳሽ ወይም ብሮውሰር አይነት እና ስሪት፣ ኦፕሬቲንግ ሲስተም እና የመተግበሪያ መሳርያን ጨምሮ ቴክኒካዊ መረጃዎችን ያጠቃልላል፡፡
  • ስለ ጉብኝትዎ መረጃን በሚመለከት የትኞቹን ገጾች እንደጎበኟቸው, ድረ-ገጹን በመጠቀም ምን ያህል ጊዜ እንደቆዩ, ወደ ድረ-ገጹ እንዴት እንደደረሱ (ቀን እና ሰዓትን ጨምሮ); የገጽ ምላሽ ጊዜ፣ የቆይታ ግዜ፣ የተከፈቱ አገናኝ ሊንኮች፣ ያወረዱት ፋይሎች እና በማውረድ ሂደት ያጋጠሙ ስህተቶች።

ኩኪዎች

የእኛ ድረ-ገጽ ሲጠቀሙ እርስዎን ከሌሎች የድረ-ገጻችን ተጠቃሚዎች ለመለየት ኩኪዎችን ይጠቀማል። ይህ ድረ-ገጻችንን ሲያስሱ ጥሩ የአጠቃቀም ተሞክሮ እንድናቀርብልዎ የሚረዳን እንዲሁም ገጻችንን እንድናሻሽል ያስችለናል። ስለምንጠቀምባቸው ኩኪዎች እና ዓላማዎች ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የኩኪ ፖሊሲያችንን ይመልከቱ።

መረጃዎችን በሚከተሉት መንገዶች ልንጠቀምባቸው እንችላለን፡፡

እርስዎ ለእኛ የሚያቀርቡልን ወይም የሚልኩልንን መረጃ እንጠቀማለን፡

  • ከእኛ በኩል የሚጠይቁትን መረጃ ወይም አገልግሎቶችን ለእርስዎ ለማቅረብ፤ስለእርስዎ አውቶማቲካሊ የምንሰበስበው መረጃ ከታች ለተዘረዘሩን አላማዎች ልንጠቀም እንችላለን፡
  • ስታቲስቲካዊ ዓላማዎችን ጨምሮ የእኛን ድረ-ገጽ ለማስተዳደር እንዲሁም የሲስተም ችግር ሲያጋጥም መፍትሄ ለመስጠት ፣
  • ለእርስዎ የምናቀርበውን የአገልግሎት ለማዘመን እና በሚጠቀሙበት ኮምፒውተር ም ሆነ ሌሎች መሳሪያዎች ማራኪና አስደሳች በሆነ መንገድ መቅረቡን ለማረጋገጥና ሲስተማችንን እንደአስፈላጊነቱ ለማሻሻል፤
  • የበይነ መረብ የደህንነት ጥንቃቄዎችን እና የድረ-ገጻችንን ደህንነት ለመጠበቅ የምናደርገው ጥረት አካል ይሆናል።
  • ይህ መረጃ በስም-አልባ ወይም ማንነትን በግልጥ ለመለየት በማያስችል መንገድ የተበሰበ በመሆኑ ግለሰብን በግል ለመለየት ከሚያስችል መረጃ ጋር የተገናኘ አይደለም። ይህንን መረጃ ለመከታተል ጉግል አናሌቲክስን እንጠቀማለን።

    Google ለየእርስዎን ውሂብ እንዴት እንደሚጠቀም ለማወቅ የሚከተለውን አገናኝ ሊንክ ሊጎበኙይችላሉ https://support.google.com/analytics/answer/6004245

    የእርስዎን መረጃ ይፋ ማድረግን በሚመለከት

    የሚሰጡን ማንኛውም መረጃ በቀጥታ ወደ እኛ ኢሜይል ይላክልናል ወይም በባለቤትነት ወይም በሊዝ ይዞታ በያዝነው ደህንነቱ በተጠበቀ ማስተናገጃ የኔትዎርክ መሠረተ ልማት እነዲሁም የኮምፒውተር ሰርቨር ላይ ሊቀመጥ ይችላል። ድረ-ገጻችንን ለማስተዳደር እንዲሁም አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ የሶስተኛ ወገን የድረ-ገጽ አስተዳዳሪ እና አገልግሎት አቅራቢን እንጠቀማለን። የእኛ ሶስተኛ ወገን አገልግሎት አቅራቢ ከአውሮፓ GDPR (አጠቃላይ የውሂብ ጥበቃ ደንብ) ጋር በተገናኘ ከፍተኛ የበይነ መረብ ጥበቃ እና የደህንነት መስፈርቶችን የሚያሟላ በመሆኑ እኛን ወክለው አገልግሎት ላይ የሚያውሉትንና የሚጠቀሙበትን ማንኛውንም መረጃ በሚስጥር እንዲያዝ ህግ ባረጋገጠው ውል ተስማምተናል። በዚህ ድህረ ገጽ በኩል ሊሰበሰብ የሚችል ማንኛውም መረጃ ደህንነቱ የተጠበቀ እና እኛ ባዘዝንበት መንገድ ብቻ የሚሰራ መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡ የእኛ አጋሮች ያለ እኛ ፈቃድ በእኛ ስም ያከማቹትን ማንኛውንም መረጃ በተለየ መንገድ መጠቀም፤ ማረም፤ መቀየር፤ ማሻሻል ወይም መሰረዝ አይችሉም።

    የእርስዎን የግል መረጃ ለሌሎች ሰዎች ወይም አጋር ላልሆኑ ድርጅጾች ወይም ኩባንያዎች አናከራይም፣ አንሸጥም ወይም አናጋራም።

    በህግ ወይም በሌሎች ደንቦች ወይም አዋጆች ካልተደነገገ እንዲሁም በህግ ተቋማት ካልተፈለገ በስተቀር የግል መረጃዎ ለክልላዊ/ብሔራዊ ተቋማት እና ባለስልጣናት እንዳይገለጽ ለማድረግ ሁሉንም የምንችለውን ጥረቶችን እናደርጋለን።

    እንደ አለመታደል ሆኖ በበይነ-መረብ በኩል የሚተላለፍ የመረጃ ስርጭት ሙሉ በሙሉ ደህንነቱ የተጠበቀ አለመሆኑ የሚታወቅ ሀቅ ሲሆን ምንም እንኳን የእርስዎን የግል ውሂብ ለመጠበቅ የተቻለንን ብናደርግም ወደ ጣቢያችን የሚተላለፈውን የውሂብዎን ደህንነት ማረጋገጥ አንችልም። አንዴ መረጃዎ እንደደረሰን ወደአልተፈለገ ቦታ እንዳይሄድ ለመከላከል ጥብቅ ሂደቶችን እና የደህንነት ተግባራትን የምንጠቀም ሲሆን ማንኛውም የሚልኩልን የመረጃ ስርጭትን በሚመለከት ሀላፊነቱ የግልዎ ይሆናል ፡፡

    የሶስተኛ ወገን ማገናኛዎች

    ድረ-ገጻችን ከጊዜ ወደ ጊዜ የሶስተኛ ወገን ድረ-ገጾች አገናኝ ሊንኮችን ሊይዝ ይችላል። ከእነዚህ ድረ-ገጾች ወደ አንዳቸውም የሚወስድ አገናኝ ሊንክ ከተከተሉ፣ እባክዎን እነዚህ ድረ-ገጾች የራሳቸው የግላዊነት ፖሊሲዎች እንዳሏቸው እና ለእነዚህ መመሪያዎች ምንም አይነት ሃላፊነት ወይም ተጠያቂነት እንደማይኖርብን ልብ ይበሉ። እባክዎ ማንኛውንም የግል መረጃ ወደ እነዚህ ድረ-ገጾች ከመላክዎ ወይም ከማስገባትዎ በፊት የነዚህን አካላት መመሪያዎች ይመልከቱ።

    የእርስዎ መብቶች - የግል አካውንቶ መረጃዎን ስለመጠቀም

    የእርስዎ የግል አካውንት ውስጥ የሚገኙ መረጃዎች በህጋዊ መንገድ እየተሰራባቸው መሆኑን የማረጋገጥ መብት አለዎት ('ወደ ግል መረጃ የመድረስ መብት ርእሰ ጉዳይ ')። ወደ ግል መረጃ የመድረስ መብት ርእሰ ጉዳይ በመረጃ ጥበቃ ህጎች እና ደንቦች መሰረት ሊተገበር ይችላል። ማንኛውም ወደ ግል መረጃ የመድረስ መብት ርእሰ ጉዳይ ጥያቄ ለሼድሊይ ሀ/የተ/የግ/ማ የህግ ክፍል በጽሁፍ መቅረብ አለበት። በዚህ መሰረት በህግ በተደነገገው የጊዜ ገደብ ውስጥ የእርስዎን የግል መረጃ እናቀርብልዎታለን። የያዝነውን ማንኛውንም የእርስዎን በአካውንቶ ውስጥ ያለ የግል መረጃ እንድንከታተል እንዲረዳን ከእርስዎ ተጨማሪ መረጃ ልንጠይቅ የምንችል ሲሆን የእርስዎን መረጃ እንዴት እንደተጠቀምንበት ቅሬታ ካለዎት፣ ወደ መረጃ ኮሚሽነር ቢሮ (ICO) ቅሬታ የማቅረብ መብት አልዎት።

    በግላዊነት መመሪያችን ላይ የተደረጉ ለውጦች

    ወደፊት በግላዊነት ፖሊሲያችን ላይ ልናደርጋቸው የምንችላቸው ለውጦችና ማሻሻያዎች በዚህ ገጽ ላይ የምንለጥፍ ሲሆን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በኢሜይል እናሳውቅዎታለን። በግላዊነት መመሪያችን ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን ወይም ለውጦችን ለማየት እባክዎ ደጋግመው የግላዊነት መመሪያ ገጻችንን ይመልከቱ።

    ግኑኝነትን በሚመለከት

    ይህን የግላዊነት ፖሊሲ በተመለከተ ያሉ ጥያቄዎች፤ አስተያየቶች፤ የማሻሻያ ሀሳቦች የምንቀበል ሲሆን ይህን ለማድረግ እንዲረዳዎ ወደ ህግ ክፍላችን ከታች በቀረበው አድራሻ መላክ ይኖርባቸዋል፡፡ legal@vyzyo.com።